ስሚ! ቆይ ለመሆኑ ሎተሪ ቢደርሰኝ ምን ታደርጊያለሽ?

ከባለቤቴ ጋር ኑሮ አልተስማማኝም፤ ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ነው፤ በሆነ ባልሆነው አገር ጉድ እስኪል እንዲሁ ስንባላ ነው ውለን የምናድረው፤ ትናንትና እቤት እንደገባሁ እነዲህ አልኳት፤-

እኔ፡ ስሚ! ቆይ ለመሆኑ ሎተሪ ቢደርሰኝ ምን ታደርጊያለሽ?

እሷ፡ ይሄ ጠማማ እድልህ አያደርገውም እንጂ፤ እውነት ቢሆንማ ህግ የሚፈቅድልኝን ግማሹን ወስጄ ከዚህ አስቀያሚ ትዳር አፈር አባትህን ጥዬህ ጥርግ እል ነበር::

እኔ፡ በጣም ጥሩ ፈጣን ሎተሪ ገዝቼ 10 ብር ደርሶኛል፤ እንኪ 5 ብርሽን ያዢና ጥፊ

*ከሆስፒታሉ ክምችት ክፍል የተገኘ* 


Print Friendly