በግዴለሽነት አስገድዶ መድፈር” የምትል አዲስ ወንጀል ፈጥሯል አሉ

ሳቅ…ከፍርድ ቤት ጓዳ

ሚስት ባሏ ከቤት ሰራተኛዋ ጋር ይማግጣል ብላ ትጠረጥራለች:: ይህን ጥርጣሬዋን በአይኗ በብሌኑ አረጋግጣ ባሏን ከነ ቅሌቱ እጅ ከፈንጅ ይዛ ለፍርድ በማቅረብ ልትበቀለው ታስብና መሻሽቶ የእንቅልፍ ጊዜ ሲደርስ ሰራተኛዋ የምትተኛበት ክፍል ውስጥ ገብታ ሰራተኛዋን መስላ ትተኛለች::

ታድያ እንደጠረጠረችው አንድ ሰው የክፍሉን በር ከፍቶ ይገባና ድምፅ ሳያሰማ አልጋው ላይ በመውጣት ከሚስት ጋር አንሶላ ይጋፈፋል:: ጉዳዩ እንደተገባደደ ሚስት አንጀቷ እየተቃጠለ “አንተ ልክስክስ ውሻ!!” ብላ በመሳደብ መብራቱን አብርታ ባሏ ላይ ለማፍጠጥ ስትሞክር ኮሽታ ሳያሰማ ገብቶ የተገናናት ዘበኛው ሆኖ አገኘችው::

እናም እንዲህ አይነት ክስ(በዘበኛው ላይ) የቀረበለት ዳኛ “በግዴለሽነት አስገድዶ መድፈር” የምትል አዲስ ወንጀል ፈጥሯል አሉ:: ጉድ ሳይሰማ ነው ነገሩ::


Print Friendly