እረፍት በዘዴ

እስቲ ከቁርስ በፊት እንቀልደው ። ቁርስዬ በዘዴ ከሸወድናት ብለን!!!

ሁለት የፋብሪካ ሰራተኞች እያወሩ ነው ።
ሳራ: ዛሬ አለቃዬን በዚም በዛም ብዬ ማስፈቀድ አለብኝ ።
አሊ : እንዴት አርገሽ?

ሳራ : ዝም ብለህ የማረገውን ተመልከት

ሳራ ኮርኒሱ ላይ ወጥታ ተንጠለጠለች ( ልክ እንደ አምፖል) በዚህ መሀል አለቃዋ ገባ ።
አለቃ: እንዴ!!! ምን እየሰራሽ ነው ሳራ ?
ሳራ : አምፖል ለመሆን እየሞከርኩ ነው ።
አለቃ : በይ በይ!!! ቀኑን ሙሉ ስትሰሪ በመዋልሽ አእምሮሽ ልክ አይመስለኝም ፤ የስራው ጫና ነው መሰለኝ ። ወደ ቤት ሄደሽ እረፍት አርጊ ሲላት አሊም ተከትሏት ወጣ
አለቃ: አንተ ደግሞ ወዴት ነህ?
አሊ : በጭለማ መስራት አልችልም ብሎት ተያይዘው ወጡ ።

እንዲህ ነው እንጂ እረፍት በዘዴ


Print Friendly