*****እወድሻለሁ*****

*****እወድሻለሁ*****

ሰውዬው ሥራ መሥራት የማትወድ በጣም ሰነፍ የሆነች ሚስት አለችው፤ ታዲያ ሚስቱ ሰነፍ መሆኗን ጠንቅቆ ቢያውቅም ተናግሮ ሊያስቀይማት ግን በፍፁም አይፈልግም፡፡ አንድ ቀን የምግብ ጠረጴዛው ላይ ያለውን አቧራ ይመለከትና ‹‹አቧራውን አፅጂው›› ብሎ ለመናገር ከብዶት ‹‹መቼም የፃፍኩትን ስታየው አቧራ መኖሩን አስተውላ ትወለውለዋለች›› ብሎ በማሰብ ጠረጴዛው ላይ በጣቱ ‹‹እወድሻለሁ›› ብሎ ይፅፍበትና ወደ ሥራ ይሄዳል፤ ከሥራ ደክሞት ሲገባ መጀመሪያ ያስተዋለው ነገር ቢኖር የምግብ ጠረጴዛውን ነበር፡፡ እሱ እንደጠበቀው አልተፀዳም፣ ይልቁንም እሱ ፅፎት ከነበረው ግርጌ ‹‹እኔም እወድሃለሁ›› የሚል መልስ ተፅፎ ጠበቀው፡፡ አያድርስ ነው፡፡


Print Friendly