“ከንደገና አገቡ ማለት ነው???

ነገሩ የሆነው ከትናንት ወድያ እሁድ ጠዋት ላይ ነው አሉ፡፡

የአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ዌንገር ቅዳሜ ለት በቼልሲ 6-0 በሆነ ውጤት ከተሸነፉ በኋላ በብስጭት እየተነጫነጩ ቤታቸው ገብተው ተኝተዋል፡፡ ከጠዋቱ አንድ ሰአት ሆኖ አላርማቸው ሲጮህም ሊሰሙት አልቻሉም፡፡

አጠገባቸው ተኝታ የነበረችው ሚስታቸውም፡- አርሴን አርሴን ተነስ እንጂ!!!

ተይኝ እስኪ ልተኛበት (አይናቸውን ሳይገልጡ ብርድልብሱን እየጎተቱ)

ሚስት፡- እንዴ አርሴን ተነሳ ባክህ 7ኮ ሆኗል (በፈረንጅ ሰአት አቆጣጠር መሆኑ ነው)

ይሄኔ አርሴን ድንብር ብለው ተነስተው “”ከንደገና አገቡ ማለት ነው???”” አሉ ይባላል፡፡


Print Friendly