የአሜሪካ፣ የእንግሊዝና የኢትዮጵያ መሪዎች ገሃነም ሆነው ነው አሉ

የአሜሪካ፣ የእንግሊዝና የኢትዮጵያ መሪዎች ገሃነም ሆነው ነው አሉ የአሜሪካው መሪ ወደ ሃገሩ ደውሎ በጣም አጭር መረጃ ይቀበላል፡፡“የአፍጋኒስታን ጉዳይ ከምን ደረሰ? አሸባሪዎችስ?” ብሎ ጠየቀ፤ ጨረሰ፡፡ ሂሳብ ሲጠይቅ 120 ዶላር ይባልና ይከፍላል፡፡የእንግሊዙ መሪ ሃገሩ ደውሎ ተመሳሳይ ጥያቄ ከጠየቀ በኋላ ዘጋ፡፡ ሂሳብ ሲል 80 ፓውንድ ተጠየቀና ከፈለ፡፡

የኢትዮጵያው መሪ ወደ ሃገር ቤት ሲደውል የአሜሪካውና የእንግሊዙ መሪዎች ወጡ፡፡ ዞረው ዞረው ደክሟቸው ሲመለሱ አሁንም እየተነጋገረ ነው፡፡ መመሪያው ፣ መግለጫው፣ ግምገማው…..ቀጥሏል፡፡

የአሜሪካውና የእንግሊዙ መሪዎች

“አሁን ከየት አምጥቶ ሊከፍል ነው? እንደፈረደብን እኛኑ አበድሩኝ ሊለን ነው እንጂ…” እያሉ ሲነጋገሩ የኢትዮጵያው መሪ ስልኩን ጨርሶ ዘጋ፡፡

ሂሳብ ሲጠይቅ የስልክ ተቆጣጣሪው 2 ብር ከ80 ሳንቲም ይለዋል፡፡

በዚህ ጊዜ የአሜሪካውና የእንግሊዙ መሪዎች በቅሬታ

“እኛ አንድ ደቂቃ እንኳ ያልሞላ ተነጋግረን ያን ያህል ከፈልን፡፡ እሱ ግማሽ ቀን ሙሉ አውርቶ እንዴት ይቺን ብቻ ይከፍላል?” ሲሉ ጠየቁ፡፡

የስልክ ተቆጣጣሪው የመለሰላቸው መልስ

“አይ የእሱ እኮ የሃገር ውስጥ ጥሪ ነው!!!” የሚል ነበር፡፡

ምንጭ፡- “ኢህአዴግን እከስሳለሁ 


Print Friendly