የእኔ እመቤት ብላክ ቦክስ ውስጥ ትርፍ ቦታ ይኖራል

የማሌዥያው አይሮፕላን የገባበት መጥፋት አንድ ቀልድ አስታወሰኝ !! ሰውየው መቼም የኢንፎርሜሽን /እውቀት / መጥፎ የለውምና ስለ ኤይሮፕሌን አሰራር ሲወራ ከሰማው ውስጥ ትኩረቱን የሳበው ይሄ ብላክ ቦክስ /black box / የሚባለው ነገር ነው ,,,,,እጅግ ጠንካራ የሆነ ከፍተኛ የሆነን የእሳት ቃጠሎን መቋቋም የሚችል ውሃ በቀላሉ የማያበላሸው ከከፍተኛ ቦታ ለይ አይሮፕላኑ እንኳን ቢፈጠፈጥ ምንም የማይሆን,,,, ብዙ ነገር ሰምቷል
እንግዲ ለመጀመሪያ ግዜ አይሮፕላን ሊሳፈር ነው የበረራ አስተናጋጆች ወደ አይሮፕላን መግቢያው በር ላይ ቆመው boarding pass እየተቀበሉ ተሳፋሪዎች ወንበር ፍለጋ እንዳይንከራተቱ አንተ በቀኝ አንተ በግራ እያሉ መጨናነቅ እንዳይፈጠር እንግዶችን ይመራሉ የሱ ተራ ደረሰ ወደ አንዷ አሰተናጋጅ ጠጋ ብሎ የእኔ እመቤት ብላክ ቦክስ ውስጥ ትርፍ ቦታ ይኖራል እንደው የመጀመሪያዬ ስለሆነ ትተባበሪኛለሽ ???

Print Friendly