አረፉ!

ፋና

image

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27፣ 2006 (ኤፍ.ቢ.ሲ.) የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድርና የኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ አረፉ።

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በታይላንድ ባንኮክ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 አመታቸው ነው ዛሬ ለሊት ሰባት ሰዓት ላይ ያረፉት።

አቶ አለማየሁ ከየካቲት 9 ቀን 2006 ጀምሮ በባንኮክ ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።

በምስራቅ ወለጋ ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው ከአቶ አቶምሳ ሚጃ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓም ነው የተወለዱት አቶ አለማየሁ።

ከኢህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የደረሰንን ሙሉ መግለጫ ከደቂቃዎች በኋላ የምናቀርብ  ይሆናል።

 


Print Friendly